Amharic Motivational Speech | Excuse | ሰበብ

ሰበብ


ስፖርት እየሰራ ያለ ወንድ
ስፖርት እየሰራ ያለ ወንድ


ሰበብ ስለ ሰዎች ፣ ክስተቶች እና ሁኔታዎች ለራሳችን የምናደርጋቸው ምክንያታዊ ምክንያቶች ናቸው። እነሱ የእኛን ባህሪ ለመከላከል እርምጃ ለመውሰድ ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ  ወይም በቀላሉ ሃላፊነትን ችላ ለማለት የምንፈጥራቸው የፈጠራ ምክንያቶች ናቸው።


  ከስር ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ😀



ምንድነው የሚያቆማችሁ? በጣም ደክሟችሃል ወይ? በቂ እንቅልፍ አላገኛችሁም እንዴ? በቂ ኃይል ዬላችሁም እንዴ? በቂ ጊዜ ዬላችሁም? ይህ ነው እንዴ እያስቆማችሁ ያለው? በቂ ገንዘብ ዬላችሁም? ያ ነው እንዴ ነገሩ? ወይስ እያስቆማችሁ ያለው ነገር እራሳችሁ ናቸሁ? ሰበብ ምክንያት ወይም ቁምነገር የሚሆነው ለሚፈጠረው ሰው በቻ ነው። ለራሳችሁ ማዘንን አቁሙ ፡፡ የሰዎችን ርህራሄና ሀዘኔታን ከመቀበል ይልቅ፣ እራሳችሁን ደግፋችሁ አንሱ። 

እራሳችሁን ከጣላችሁበት ቦታ አንሱ፡፡ አንድ ሰው የሕይወቱን ጥግ ድረስ በ 6 ወይም 7 ኮከብ ሆቴል በተንከባለለ ሮልስ ራይስ ውስጥ ብታየው በእሱ ላይ አትቅናበት፡፡ ምክንያቱም እሱ ይህን ያገኘው ለፍቶ እና ደክሞ ስለሰራ ነው፡፡ ማንም አንዳች ነገር አልሰጠውም ፡፡ እናስ ምን እያደረጋችሁ ነው፡፡ በሉ ከእንቅልፋችሁ ተነሱ። ያ ውስጣችሁ ያለውን አንበሳ አንቁት። ጨዋታ በርትቷል። ጊዜው አሁን ነው፡፡ በአገራችሁ እና በማህበረሰባችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ተደራሽነት እና ሀብቶች ለመጠቀም ጊዜው አሁን ነው ፡፡ 



Photo of a man working out
ጠንካራ ስፖርተኛ



በሕይወታችሁ ውስጥ ችግር ገጥሟችኋል? በአካባቢያችሁ ላይ ችግር ገጥሟችኋል? እንግዲያውስ ለዛ ነገር መፍትሄ ፈልጉለት። አንድ ነገር አድርጉ። ከፈለጉ ያን ነገር ለማግኘት ጣሩ። ዝም ብሎ ሰበብ መደርደር መፍትሔ እንዳልሆነ እወቁ፡፡ እነሱ የራሳችሁ አዕመሮ የፈጠረው የቀረፀው ውሸቶች ናቸው። እና እንዲህ ካልን ውሸቶችን እንዴት ማስቆም ይቻላል? ውሸቶችን ማስቆም የሚቻለው እውነቱን ስንጋፈጥ ነው ፡፡ እናም እውነታው ጊዜ አላችሁ ብቃቱ አላችሁ እውቀቱ አላችሁ የማድረግ ወኔውም አላችሁ። በሕይወት ውስጥ የመልካም ነገሮች ሁሉ ፍሬ በችግር ይጀምራል ፡፡ ሁሉም ነገር ዋጋ ያለው ነው ፡፡ እናም ዝም ብሎ ወደናንተ አይመጣም፣ ዝም ብሎ በእቅፋችሁ ውስጥ አይሆንም እናም ኡፍ ቀላል ነበር የምትሉት አይሆንም ሁሌም ቢሆን ከባድ ነው የሚሆነው፡፡ 

ያንነገር ከፈለጋችሁት ለፍታችሁ ማግኘት ይኖርባችኋል። ይህ የእናንተ ዕድል ነው ፡፡ ይህ የእናንተ ብቸኛ ሙከራ ነው። ይህ የእናንተ ሰዓት ነው። ይህ የእርስዎ ጊዜ ነው። ይህ የእናንተ ቦታ ነው ፡፡ ይህ የእናንተ አጋጣሚ ነው ፡፡ ዛሬ የእናንተ ጊዜ ነው። ነገ ፣ ነገ ፣ ነገ ማለታችሁን አቁሙ፡፡ ዛሬ እንጂ ነገ የሚባል ነገር ዬለም። ይህ ህልማችሁ ነው። ማግኘት፣ መድረስ ከፈለጋችሁ ለማንም የማይጠቅመውን ጣታችሁን መቀሰር አቁሙ። ዝም ብላችሁ ሰበብ መደርደር አቁሙ። ማንም ቢሆን የናንተን ህልም እንኩ ብሏችሁ የሚሰጣችሁ አይኖርም። ወደ ስኬት ሩጡ። ወደፊት ግፉ። ምክንያቱም ሰበብ መደርደር ለናንተ እንጂ ማሳካት ለፈለጋችሁት አላማ ዋጋ ዬለውም።

Translated By Google :

Excuses are rational reasons for people, events, and circumstances. They are creative reasons to postpone action or simply ignore responsibility.

What stops you? Are you too tired? Didn't you get enough sleep? Do you have enough energy? Do you have enough time? Is this what is stopping you? Do you have enough money? Is that so? Or are you the one who is stopping you? The cause or effect is only for the person being created. Stop feeling sorry for yourself. Instead of accepting people's compassion and sympathy, support yourself.


Get rid of clutter. If you see a person in a 6 or 7-star hotel rolling on the edge of his life, don't be jealous of him. Because he got it because he worked hard. No one gave him anything. And what are you doing? Eat, wake up. Ignore that lion inside you. Game intensified. The time is now. Now is the time to take advantage of the access and resources available in your country and community.

Are you having problems in your life? Are you having trouble in your area? So find a solution to that problem. Do something. Try to find that thing if you want to. Understand that excuses are not the answer. They are fabricated lies created by your own mind. And if so, how can we stop lying? Lying can be stopped when we face the truth. And the fact is, you have time, you have the ability, you have the knowledge, you have the courage to do it. The fruitage of all good things in life begins with trouble. Everything is valuable. And it doesn't just come to you, it just doesn't fit in your lap and you can't say it was easy.

If you want something, you have to get it right. This is your chance. This is your only attempt. This is your time. This is your time. This is your place. This is your opportunity. Today is your time. Stop saying tomorrow, tomorrow, tomorrow. There is no such thing as tomorrow. This is your dream. If you want to get it, stop pointing your finger at no one. Just stop making excuses. No one will even give you a dream. Run to success. Push forward. Because making excuses is important to you, not to you.

Post a Comment

0 Comments