ለብዙ ሰዎች እርግዝና ትልቅና አስደሳች ነገር ነው። በዛው ልክ ግን አስጨናቂ እና አስደንጋጭ ሊሆን ይችላል። በተለይ በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ላረገዘ ሰው ፈታኝ ነው የሚሆነው። እናም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፣ ምን አይነት ስሜት እንዳለውና ምን አይነት ምልክቶችን ልናይ እንችላለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ይነሣሉ። ስለሆነም ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ከፈለጋችሁ ትክክለኛው ቦታ ላይ ናችሁ።
ምንም
እንኳን አንዲት ሴት እንዳረገዘች ወይም እንደ ፀነሰች የምታውቀው በህክምና ቢሆንም ነገር ግን ሌሎች ምልክቶችም የእርግዝናው አመላካች ሊሆኑ ይችላሉ። የመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ምልክቶች የወር አበባ ከመቆም በላይ ናቸው። ለምሳሌ : የማቅለሽለሽ ፣ ለተለያዩ
ሽታዎች ምላሽ መስጠት ፣ ድካም ሊሆኑ ይችላሉ።
የመጀመሪያዎቹ
የእርግዝና ሳምንታት በማይታይ ፣ ነገር ግን አስገራሚ ለውጦች የሚታዩበት ወቅት ነው። እናም በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ ምን ዓይነት አካላዊና ስሜታዊ ለውጦች እንደሚጠብቁ ካወቁ በሚቀጥሉት ጊዜያት በልበ ሙሉነት ለመቋቋም ወይም ለመቀጠል ይረዳዎታል
- ድካም
- የውሀ ሽንት መጨመር
- ቃር
- የሆድ ድርቀት
- የጡት መጠን መጨመር
- ብዥታ ከማስመለስ ጋር ወይም ለብቻው
- የምግብ ፍላጎት መቀያየር
1, ድካም
በመጀመሪያዎቹ
የእርግዝና ወቅት ፣
"ፕሮጄስትሮን"
የተባለው ሆርሞን መጠን ከፍ ይላል። ይህም እንቀልፍ እንቅልፍ እንዲሎት ያደርጋል። እናም በዚህ ጊዜ በተቻላችሁ መጠን እረፍት ማድረግ ይኖርባችኋል። ጤናማ አመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጉልበትዎን ሊጨምር ይችላል። ስለሆነም እኚህን በመተግበር ይህን ጊዜ ማለፍ ይቻላል።
2, የውሀ ሽንት መጨመር
ከተለመደው ጊዜ በበለጠ መልኩ መፀዳጃ ቤት መጠቀሞን ሊያስተውሉ ይችላሉ። በእርግዝና ወቅት በሰውነት ውስጥ ያለው የደም መጠን ይጨምራል, ይህም ኩላሊቶችዎ በሽንት ማጠራቀሚያ ውስጥ የሚያስቀምጡት የሽንት ወይም የፈሳሽ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።ስለሆነም በተደጋጋሚ ሽንት ቤት (መፀዳጃ ቤት) ልትመላለሱ ትችላላችሁ።
3, ቃር
በጨጓራ
እና በጉሮሮ መካከል ያለውን ቫልቭ ለቀቅ የሚያደርጉ የእርግዝና ሆርሞኖች ፣ የሆድ አሲድ ወደ ጉሮሮ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ቃር ያስከትላሉ። ቃር እንዳይከሰት የሚፈልጉ ከሆነ በትንሽ እና
በተደጋጋሚ ምግቦችን ይመገቡ። በተጨማሪም የተጠበሱ ምግቦችን ፣ ፤"ሲትረስ" ፍራፍሬዎችን ፣ ቸኮሌት
እና ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን ይራቁ።
- ሲትረስ ፍራፍሬዎች ማለት የተለያዩ የፍራፍሬ ዘሮች ናቸው። ለምሳሌ ብርቱካን ፣ ሎሚ ፣ የወይን ፍሬን የሚያካትቱ ናቸው።
4, የሆድ ድርቀት
ከፍ
ያለ የ"ፕሮጄስትሮን" ሆርሞን የምግብ መፍጫ ስርዓትን በማቀዛቀዝ የምግብ እንቅስቃሴን ሊቀንስ ይችላል ፣ ይህም የሆድ ድርቀት ያስከትላል። የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ወይም ለማስታገስ በአመጋገብዎ ውስጥ ብዙ ፋይበርን ያካትቱ። በተጨማሪም ብዙ ፈሳሾችን በተለይም ዉሃ እና ፕሪም ወይም ሌላ ፍራፍሬ ጭማቂዎችን ይጠጡ። መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲሁ የሚረዳ ነገር ነው።
- ፋይበር ማለት ሰውነታችን ሊያዋህደው የማይችል የካርቦሀይድሬት ዓይነት ነው። ፋይበር የሰውነታችንን የስኳር አጠቃቀም ለመቆጣጠር ይረዳል።
5, የጡት መጠን መጨመር
6, ብዥታ ( እንደማዞር ) ከማስመለስ ጋር ወይም ለብቻው
7, የምግብ ፍላጎት መቀያየር
ነፍሰጡር በሚሆኑበት ጊዜ ለተወሰኑ ሽታዎች የበለጠ ስሜታዊ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም ለምግብ ያሎት ስሜት ሊቀያየር ይችላል። ልክ እንደአብዛኛዎቹ የእርግዝና ምልክቶች የምግብ ምርጫዎቾ በሆርሞኖቾ መለዋወጥ ላይ የሚመረኮዝ ይሆናል ማለት ነው።- Fatigue
- Increased urination
- Heartburn
- Constipation
- Increased breast size
- Nausea with or without vomiting
- Changes in appetite
0 Comments