ምስጥራዊ ሊያደርጓቸው የሚገቡ 8 ነገሮች | Things you should keep Secrets in Amharic


በእለተ እለት እንቅስቃሴያችን ወቅት የተለያዩ አጋጣሚዎች፣ የተለያዩ ሁኔታዎች፣ የተለያዩ ክስተቶች ያጋጥሙናል። ይህም ያጋጠሙንን ነገሮች ለሰዎች ማጋራት ልያምረን ይችላል። ነገር ግን የምንተነፍሳቸው ቃላቶች በመጀመሪያ ደረጃ ከማውራታችን በፊት ለሰሚ ጆሮ ከመድረሱ በፊት መገምገም ያስፈልገናል። እናም በዚህ ጽሁፍ ሁልጊዜ ምስጢራዊ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ስምንት ነገሮችን በሚል ርእስ ስር የዳሰስነውን ይዘንላችሁ መተናል፣ አብራችሁን ቆዩ። 


ከስር ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ😀





1, የናንተን ምስጥርና ስለሌሎች የምታውቁትን አሳፋሪ ነገሮች 

ምስጥር (a photo of a man say shh)
ምስጥር


በመጀመሪያ ደረጃ ሰውን ማማታቺሁ መቼም ቢሆን ጥሩ ሰው አያረጋችሁም::  በዚህ መንገድ ሁልጊዜ በራስ መተማመን እንደሌላችሁና የሌሎቹን እሴት በማቃለል እራሳችሁን በተሻለ ሁኔታ ላይ ያላችሁ እንደሆነ ለማስመሰል ታሳያላችሁ በተጨማሪም  መርሳት የሌለባችሁ ነገር አሉታዊ መረጃን ስትናገሩ ከአሉታዊ ኃይል ጋር እንደሚመጣም እወቁ:: ይህ ደግሞ በናንተ ወይም በማችሁት ሰው ላይ መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል::  ስለዚህም  ስለአንድ ሰው የምታውቁት መጥፎ ነገር ካለ ለራሳችሁ ብቻ ያዙት ወሬዉን ወይም ሀሜቱን ማሰራጨት አያስፈልግም ::


 2,  ስለ ንብረታችሁ

a photo of Money


አንዳንድ ሰዎች  አዲሱ መኪና ቤት ልብስ ወይም ሌላ ገንዘብ ሊገዛ የሚችለውን ማንኛውንም ነገር ሲገዙ ጉራቸውን ለመንዛት እስከሚጀምሩ ድረስ መጠበቅ አይችሉም:: ሆኖም ግን እንደዚህ አይነት ባህሪ ለራሳችን ከፍ ያለ ግምት እንደሌለን አመላካቾች ናቸው:: ገና ብዙ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ትልቅ የባህሪ ጉድለቶች ያላቸው ናቸው:: ጉድለታቸውን ለመደበቅና ትኩረት ለመፈለግ ቁሳዊ ንብረትን ይጠቀማሉ:: ጉራ ለመንዛት አትቸኩሉ እናም ንብረታችሁን ለአደባባይ በማሳየት ለራሳቸው ያላቸውን ዝቅተኛ አመለካከት አታሳዮ::


3, ምን ያህል ገቢ እንደምታገኙ

a photo of Money


የናንተ ገቢ በርግጥም ሌሎች ሊያቁት የማይገባ ነገር ነው:: ስለገንዘብ ማውራት ብዙ ደስ የማይል ነው :: ምክኒያቱም የምታወሩለትን ሰው የገንዘብ ሁኔታ በጭራሽ እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል:: እናም ምናልባት ስለ ገንዘባቸው የሚያወሩ ሰዎች መሀል ራሳችሁን ካገኛችሁ እነሱ በጣም ደህንነት የማይሰማቸው ና የማያቋረጥ የሰዎችን ማረጋገጫ የሚሹ ናቸው:: እናም እነዚህ ዓይነት ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ከገንዘብ ውጪ ምንም ፍላጎት የሌላቸው ናቸው::


4, የወደፊት ግቦቻችሁ

እቅድ (a photo of planning)
እቅድ


በህይወታችሁ እና በስኬታችሁ መኩራትና መደሰት ፍፁም መደበኛና ጥሩ ነገር ነው:: ጥናቶች አንዳሳዩት ግቦቻችሁን ለሌሎች ሰዎች ሳታጋሩ ዝም ብላችሁ ስራችሁን የምትሰሩ ከሆነ በእርግጥም አላማችሁ ላይ ትደርሳላችሁ:: በተጨማሪም አንዳንድ ጥናቶች እንዳሳዩት ግቦቻችሁን ለሌሎች ሰዎች ማጋራት ወደነሱ የመድረስ እድላችሁን ይቀንሳል ብለዋል:: ይህ ደሞ አምራችንን ግቦቹን ቀድሞ እንዳሳካና ወደ ስኬት ጠንክሮ ለመስራት ያለንን ወኔ የሚቀንሱ የውሸት የጥረት ስሜቶችን በመስጠት ያሳስቱናል:: ስለዚህ ምግቦችአችንን ለራሳችን ብንይዛቸው ይመረጣል:: 


5, ለሌሎች መልካም ነገሮችን ማድረግ

መርዳት (a photo of a man helping)
መርዳት


የጎዳና ተዳዳሪ የታመመ ሰው ወይም ወላጅአልባ ህፃናትን ስለረዱ ሰዎች በማህበራዊ ሚድያ ላይ በቪዲዮ ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል:: ምንም እንኳን የተገሩ ሰዎችን መርዳት ሁልጊዜም ጥሩ ሐሳብ ቢሆንም ነገር ግን ደሀውን ማህበረሰብ ተጠቅሞ በማህበራዊ ሚዲያ መልቀቅ ለራሳችሁ ጥቅም እንጂ ለድሃው ታይቶ ስለማይቆጠር ባታደርጉት ይመረጣል:: ነገር ግን እንዳትሳሳቱ ቪዲዮችን ለቃችሁ  የበለጠ እርዳታ ለማሰባሰብ ከሆነ ይህ ሌላ ርዕሰ ጉዳይ ነው:: ስለዚህ መልካም ስራዎች ሳይነገሩ ሲቀሩ ዋጋ አላቸው::


6, እምነታችሁንና ምርጫዎቻችሁን

ሃሳብ (opinion photo)
እቅድ


ሁላችንም በተለያዩ ነገሮች እናምናለን እናም በህይወት ውስጥ የተለያዩ ምርጫወች አሉን:: የራሳችን ምርጫዎች እምነቶችና መርሆች ያን ያህል መጥፎ ርዕሰ ጉዳይ ባይሆኑም አንዳንድ ሰዎች በጣም ርቀው በመሄድ በሌሎች ላይ ለመጫን ይሞክራሉ::  ይህንን ማድረግ የሌሎችን ሰዎች ሃሳብና እምነት አለማክበራቸው ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም ሰዎች ሊያቀርባቸው አይሞክሩም:: ስለዚህ ሃሳቦቻችሁን አንስታችሁ መወያየት ካለባችሁ የሌሎችንም ስሜት ባከበረ መሆን አለበት::


7, ምን ያህል ጀግና እንደሆናችሁ

ጀግና (a photo of brave)
ጀግና


እውነተኛ ጀግና የጀግንነቱን ድርጊቶች በጭራሽ አያጋራም:: ምናልባትም በፊልሞች ውስጥ የምናያቸው አብዛኞቹ አክተሮች ጭምብል ለብሰው ማንነታቸውን ለመደበቅ የሚሞክሩት ለዚሁ ነው:: ጀግኖች ማድረግ ያለባቸውን ነገር የሚያደርጉት እንዲነገርላቸው ወይም እንዲወራላቸው ሳይሆን በአላማቸዉ የሚያምኑ ቆራጥና መልካም አሳቢ ሰዎች ስለሆኑ ነው:: እራሳችሁን እንደ ጀግና የምት ቆጥሩ ከሆነ እናንተ ስለራሳችሁ እንድታወሩ ሳይሆን ሌሎች እንዲያወሩ ታደርጋላችሁ::


8, የቤተሰብ ጉዳዮች

ቤተሰብ (a photo of a family)
ቤተሰብ


ችግር የሌለበት አንድም ቤተሰብ የለም:: አንዳንዶቹ ትላልቅ አንዳንዶቹ ደግሞ ትናንሽ ናቸው:: ምንም ቢሆን ግን ሁላችንም ጋር ያሉ ነገሮች ናቸው:: እነዚህን ችግሮች ለማያውቃቸው ሰዎች ጋር ማጋራት በጭራሽ አይፈታቸውም:: ስለዚህ እነሱን ማውራት ያለባችሁ ብቸኛዎቹ ሰዎች ባለጉዳዮቹ ማለትም ቤተሰቦቻችሁ ናቸው:: እኝህን ጉዳዮች ለሌሎች ማካፈል አሉታዊነቱን ይጨምራል:: ሌሎች ሰዎች እንዲያዝኑላችሁና በቅርብ ሰዎች ምክር ማግኝት የሚሉ ሁለት ሀሳቦች የተለያዩና የተራራቁ ናቸው:: ስለዚህ ማዉራት ያለባችሁን ሰው በደንብ ማወቅ ይኖርባችሃል::


Translated by Google


During our daily activities, we may encounter different situations, different situations, different events. This can make it easier for us to share our experiences with others. But the words we breathe must first be evaluated before they can be heard. So stay tuned for the eight things you should keep in mind in this article.

1, Your secret and the embarrassing things you know about others


First of all, confusing people will never make you a good person. In this way, you show that you are not always confident and that you are in a better position by underestimating the values of others. This can have a detrimental effect on you or anyone else. So if you know something bad about someone, you don't need to keep it to yourself.

2, About your property


Some people can't wait until they start bragging about buying new clothes, clothes, or anything else that money can buy. However, such behavior is an indication that we do not value ourselves highly. It is often the case that such people have serious personality flaws. They use material possessions to hide their shortcomings and seek attention. Do not rush to boast and do not show low self-esteem by displaying your property.


3, How much income you make

Your income is really something that others should not be aware of. Talking about money is very unpleasant. This is because it is impossible to be sure of the financial situation of the person you are talking to. And maybe if you find yourself in the middle of someone talking about their money, they are very insecure and constantly looking for reassurance. And these kinds of people have no interest in money other than life.


4, Your future goals

It is perfectly normal and good to be proud and happy in your life and success. Studies show that if you do your work without sharing your goals with other people, you will achieve your goal. He also said that some studies show that sharing your goals with other people reduces your chances of reaching them. This, in turn, misleads us by giving us false impulses that undermine our motivation to achieve our goals early and to work hard for success. Therefore, it is better to keep our food for ourselves.


5, To do good to others

It is common for people living on the streets to watch videos on social media about people who have helped children or orphans. Although it is always a good idea to help the underprivileged, it is better not to do so because it is not for the benefit of the poor but for the benefit of the poor. But don't get me wrong, if you leave videos to get more help, this is another topic. Therefore, good deeds are valuable when they are not mentioned.


6, Your beliefs and choices

We all believe in different things and we have different choices in life. While the beliefs and principles of our own choices are not so bad a topic, some people go too far and try to impose it on others. Doing this not only disrespects other people's thoughts and beliefs but also does not try to present them to others in the future. So if you have to discuss your ideas, you have to respect the feelings of others.


7, How brave you are

A true hero never shares his heroic deeds. Maybe that's why most of the actors we see in movies try to hide their identities. Heroes do what they are supposed to do, not because they are told or talked about, but because they are determined and good people who believe in their purpose. If you consider yourself a hero, you will make others talk, not talk about yourself.


8, Family Matters

There is no family without problems. Some are big and some are small. No matter what, they are all with us. Sharing these problems with strangers will never solve them. So the only people you have to talk to are the clients, your family. Sharing these issues with others increases the negative. The idea of getting other people to grieve for you and getting advice from people nearby is different and different. So you need to know the person you are talking to.

Post a Comment

0 Comments