በአንድ ወቅት በጣም ቁጡና ተናዳጅ ልጅ ነበር… Short Amharic Story

 ከስር ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ😀






በአንድ ወቅት በጣም ቁጡና ተናዳጅ ልጅ ነበር ፡፡ የልጁ አባት አንድ ትምህርት ሊያስተምረው ፈለገ ፣ ለዚህም ሲል በውስጡ ምስማር የያዘ ከረጢት ይሰጠዋል እናም በንዴት በጦፈ ቁጥር በእንጨት አጥር ውስጥ ምስማሩን መምታት እንዳለበት ይነግረዋል፡፡ በዚህም የትምህርት ቆይታው፣ በመጀመሪያው ቀን ልጁ 37 ምስማሮችን የእንጨቱ አጥር ላይ መቶ ነበር ፡፡ በጣም በቁጣ ገንፍሎ ነበር ማለት ይቻላል። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ልጁ ቁጣውን መቆጣጠር ጀመረ ፣ በዚህም የተነሳ በአጥር ውስጥ ያሉት የምስማሮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ጀመረ። ወጣቱ ልጅ እነዚህን ምስማሮች ወደ አጥር ከመምታት ይልቅ ንዴቱን መቆጣጠር ቀላል መሆኑን ያገኘው ብዙም ሳይቆይ ነበር፡፡ ከዚያ ፣ ልጁ አንድ ጊዜ እንኳን ቁጡነትን የማያስቆጥርበት ቀን መጣ ፣ እናም በእራሱ በጣም ኮራ ፣ ለአባቱ ለመናገር በጣም ተቻኮለ፡፡ አባቱም በነገረው ነገር በጣም ተደሰተ። እናም ልጁ ቁጣውን ጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ፣ ቁጣውን መቆጣጠር በቻለበት ቀን ሁሉ አንድ አንድ ምስማር ከእንጨቱ አጥር እንዲያወጣ ሐሳብ ያቀርብለታል፡፡ ብዙ ሳምንታት አለፉ እናም ወጣቱ ምስማሮቹ ሁሉ እንደጠፉ ለአባቱ ለመንገር የቻለበት ቀን በመጨረሻው ደረሰ፡፡ ከዛም በጣም በእርጋታ አባትዬው ልጁን በእጁ ይዞት ወደ አጥሩ ይወስደዋል፡፡ "ልጄ ፣ በጣም ጥሩ አድርገሃል" ፈገግ በማለት እያናገረው  "ነገር ግን በአጥር ውስጥ ያሉትን ቀዳዳዎች ተመልከት ፡፡ አጥሩ በጭራሽ ተመልሶ እንደነበረው ዓይነት አይሆንም።" ልጁም አባቱ እየነገረው ያለን ነገር በጥሞና እያዳመጠ ነበር፡፡አባቱም መናገሩን ቀጠለ "በቁጣ ነገሮችን ስትናገር እንደነዚህ ያሉትን ቋሚ ጠባሳዎችን ይተዋሉ። እናም ምንም ያህል ጊዜ ይቅርታ ብትጠይቅም ቁስሉ ግን አሁንም እዚያው ይቀራል፡፡" በዚህ ጽሁፍ ዋጋ ካገኙበት እባክዎን የበለጠ እንደዚህ አይነት ስራዎችን መስራት እንድንችል ዘንድ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ማጋራት እንዳትረሱ።


Translated by Google


There was once a very angry boy. The boy's father wanted to teach him a lesson, so he was given a bag with nails in it and told him to hit the nail on the wooden fence every time he got angry. During this time of the study, on the first day, the boy had 37 nails on the wooden fence. He was very angry. Over the next few weeks, the boy began to control his temper, and the number of nails in the fence began to plummet. The boy soon learned that it was easier to control his temper than to push the nails into the wall. Then came the day when his son was no longer angry, and he was so proud of himself that he hurried to tell his father. His father was very pleased with what he said. He advises the boy to take a nail out of the wooden fence as long as he can control his anger. Several weeks passed and the day finally came when the young man was able to tell his father that all his nails were gone. Then, very slowly, the father took his son by the hand and led him to the fence. "My child, you have done very well," he said with a smile, "but look at the holes in the fence. The fence will never be the same as it used to be." The boy was listening intently to what his father was saying. If you are interested in this article, please do not forget to share it with your friends and relatives so that we can do more of this work.

Post a Comment

0 Comments