ከስር ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ😀
ባለማችን ላይ በአሁኑ ሰዓት ብዙ ሰዎች አዲስ ነገር መሞከርን በጣም ይፈራሉ:: አዲስ ነገር ከመሞከር ይልቅ በደህንነት ክልላቸው መሆንን እመርጣሉ:: ነገር ግን ታዋቂ አባባል እንደሚለው ከሆነ አዲስ ነገር መሞከርን መፍራት እራሱ ትልቅ ፈተና ነው:: እናም በዛሬው ቪድዮ በየቀኑ ልንሞክራቸው የሚገቡ 5 አዳዲስ ነገሮች ብለን ያሰብናቸውን ይዘንላችሁ መተናል::
1, እራሳችሁን መሆን
ማንነት |
ግልጽ ስለሆናችሁ ብቻ ሰዎች ስለእናንተ የተለየ ነገር ያስባሉ ብለው ይፈራሉን? ሰዎች ሊጠሉኝ ይችላሉ ብላችሁ ፈርታችሁነውን? እንግድያውስ ልንገራችሁ የዚች ህይወት አንደኛ እውነታዋ ሁሉም ሰው እንዲወዳችሁ መጠበቅ የለባችሁም:: እናንተ ብርቁ ና አምሳያ የሌላችሁ ፍጡራን ናችሁ፡፡ እናም ሁሉም ሰው ይህንን ላያስተውል ይችላል:: ትልቁ ነገር ለራሳችሁ ያላችሁ አመለካከት ነው:: አንድ ሰው የናንተን ማንነት ካልወደደው የናንተ ጥፋት አይደለም:: ይህ ማለት ግን ስለራሳችሁ ያላችሁ አስተሳሰብ ሁሉ ትክክለኛ ነው ማለት አይደለም ደካማና መጥፎ ጎን ሊኖራችሁ ይችላል:: ይህም የሚያሳየው ሰው መሆናችሁን ብቻ ነው::
ብዙን ጊዜ ሰዎች ሰውን አስደሳች ብቻ ይሆናሉ:: ሌላኛው ወገን እንዲዝናናና ሁሌም ከነሱጋ ለመደሰት ሲባል ራሳቸውን ይጥላሉ:: ነገር ግን መርሳት የሌለባችሁ ነገር እውነተኛ ማንነታችሁን ይዛችሁ መጠበቅ እንዳለባችሁ ነው:: እውነታውን ሌላኛው ሰው ስላላየው ብቻ የናንተ ዋጋ ይቀንሳል ማለት አይደለም:: የናንተ ዋጋ የሚቀንሰው ለሰዎች እውነተኛ ማንነታችሁን ያላሳያችሁ ጊዜ ነው:: እናም እባካችሁ ተጠንቀቁ ለሰዎች ደስታና ለሰዎች ርካታ ስትሉ እውነተኛ ማንነታችሁን እንዳትተው:: እናም የናንተን እድገትና የናንተን ጥሩ ጎን የምትመኙ ከሆነ ወሳኞቹ እናንተና እናንተ ብቻ ናችሁ::
2, ያለምንም ክፍያ ሰዎችን መርዳት
መርዳት |
ህይወት ብዙ ትርጉም አላት:: የምንትረጉሙበት መንገድ ደግሞ የራሳችን ና የራሳችን ብቻ ነው:: ደስታ የሚመጣው ከራሳችን ውጭ ስናስብ ነው እንጂ እኔ ብቻ የምንል ከሆነ አይደለም:: በዚህ ህይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት
ነገር በህይወታችን ውስጥ ጥሩም ይሁን መጥፎ ካረግን ዞሮ ክፍያውን እንደምናገኝ ነው:: ምላሽን ሳትጠብቁ በዕለተ እለት ህይወታቸሁ ፍቅር
መስጠትን ልመዱ:: ባሁኑ ሰአት መልሰው ሊከፍላችሁ ለማይችሉ ሰዎች ብዙ ስጣቸው:: መስጠት ማለት ለገንዘብና ለቁሳዊ ነገር የተገደበ ብቻ አይደለም:: ለምሳሌ መልሰው ፈገግ ሊሉላችሁ ለማይችሉ ሰዎች ፈገግ በሉላቸው::
ዓይናፋርና ፈሪ የሆኑ ሰዎችን አደፋፍራቸው ሞራል ስጧቸው:: ሌሎች ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ደስታን እንዲያገኙ ከረዳችሁ
በናንተ ህይወት ውስጥ ደስታ ሲባዛ ታያላችሁ::
3, የድርጊቶቻችሁን ውጤት መቀበል
ሃላፊነት |
የሆነ ስተት ስትሰሩ እንዴት ነው የምትሆኑት:: ሀላፊነት ትወስዳላችሁ ወይስ አጠገባችሁ ያለውን ሰው ወይም ሁኔታዎች ላይ ታስባላችሁ:: ብዙ ሰዎች ስለ ህይወት ያልተረዱት ነገር ቢኖር ከዚህ በፊት ላረግናቸው ነገሮች ሀላፊነቱን የምንወስድ ከሆነ ለምናስበው የወደፊት ህልማችን መድረሳችን የማይቀር ነው:: ነገር ግን አሁን ያላችሁበትን ሁኔታ በሌሎች ሰዎች ላይ የምትለጥፉ ከሆነ ወደፊትም ቢሆን ኃላፊነትን መውሰደ የማትሹና የማትፈልጉ ናቸሁ:: ሌሎች ነገሮችን ሰበብ ማድረግ የማይረባ ምክንያት የመፈለግ መንገድ ነው:: ለነገሮች ዝምብላችሁ ሰበብ መደርደር ለውድቀታችሁ የመጀመሪያው መንገድ
ነው:: ለውሳኔያችሁ እናንተና እናንተ ብቻ ናችሁ ኃላፊነት መውሰድ የሚገባችሁ:: አንዳንድ ውጤቶች ደስ የማይሉ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሁሌም ቢሆን የኔ ሃላፊነት ነው ብላችሁ በየቀኑም በራሳችሁ ላይ ለውጥ ማምጣት ይኖርባቸዋል:: ምክንያቱም ውጤቶች የድርጊቶች አካል ናቸውና:: ለምትሠራቸው እንቅስቃሴዎች ሃላፊነት የምትወስድ ከሆነ የበለጠ አዲስ ነገር በመማር ራሳችሁ ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ::
4, ለሚያጋጥሙን መጥፎ ነገሮች ክፍት መሆን
መድፈር |
በሆነ ጊዜ ላይ እምነት የጣልንባቸው ሰዎች እንኳ ስሜታችንን የሚጎዱ ሆነው ልናገኛቸው እንችላለን:: ልባችን ይሰበራል:: ምናልባትም እንናንተም ጭምር የሌላውን ሰው የሰበረችሁበት ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ:: ምናልባትም በሆነ ጊዜ ከጓደኞቻቸሁ ጋር ልትጣሉ ትችላላችሁ:: ምንአልባትም ከምትወዳቸው ሰዎች ጋር
ተጣልታችሁ ወይኔ ላጣቸው
ነው ብላችሁ ልትፈሩ ትችላላችሁ:: ወይም ባላሰባችሁት ሰዓት የምትወዱትን
ሰው ልታጡ ትችላላችሁ:: እኝህ ክስተቶች የህይወት አንድ አካል ስለሆኑ በሙሉ እና በክፍት ልብ ልንቀበላቸው ይገባል:: ብዙ ሰዎች ራሳችንን ለነገሮች ክፍት ማረግን እንደ ድክመት ይቆጥሩታል:: ነገሮችን ለመጋፈጥ የሚደፍሩ ጥቂት ሰዎች ናቸው:: ህመም እንዳይሰማችሁ ልባችሁን መድፈን ለመኖር ጥሩ ነው ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ። ነገር ግን ልብን ደፍኖ መኖር ማለት ልክ እንዳለመኖር ነው። ማንኛውም
ሰው በህይወት እስካለ እና መውደድ እስከቻለ ድረስ በሆነ ሰአት መጎዳቱም አይቀሬ ነው። እናም ለነዚህ ነገሮችን ልባችሁን ክፍት ማረጋቹህ በህይወታችሁ ውስጥ ቅንነትንና ታማኝነት እንዲኖር ያረጋል:: እናም ሳቁ በህይወታችሁ ውስጥ ምንም አይነት ነገር እንዳልነካችሁ ተደሰቱ:: ቀናችሁ
በህመም ሊያልቅ ይችላል ብላችሁ ሳይሆን መፍራት ያለባችሁ በፍቅርና በታማኝነት ላይጀምር ሊችል ይችላል ብላችሁ መሆን አለበት:: ህይወት አጭር ነች:: ለተለያዩ ህመሞች
ራሳችሁን ክፍት ማረግና በሙሉ ልብ ልትቀበሏቸው ይገባል:: ምክንያቱም ለራሳችን ታማኝ መሆንና ፈተናዎችን መጋፋጣችን ትልቅ ደረጃ ያደርሰናል::
5, የማታውቁትን ነገር አላቅም በሉ
ብዙ ሰዎች የማያውቁት ነገር አቃለሁ በማለት ብዙ ነገሮችን ያበላሻሉ:: እውነት ለመናገር አንድን ነገር አላቅም ብትሉ ምን ልታጡ ትችላላችሁ:: ጓደኞቻችሁ ይስቁባችኃልን? ወይንስ በዛን ሰዓት ክብራችሁ የወረደ ይመስላችኋልን? ማወቅ ያለባችሁ ግን እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚዎችን የምታሳልፉት በዛን ሰዓት ብቻ ነው:: አላቅም ብትሉ አዲስ መረጃና አዲስ ነገር ስለምታገኙ እውቀታችሁን እያሰፋችሁ ትመጣላችሁ:: ምናልባትም የሚስቁባችሁ ጓደኞቻችሁ ምንም የማያውቁ ሊሆን ይችላል:: እውቀት በቀላሉ የምታገኙት ነገር ነው:: ይህ የሚሆነው ግን ስትጠይቁ ብቻ ነው:: እናም በሂወታቸው ማደግና መለወጥ የምትፈልጉ ከሆነ አዲስ ነገር ለማወቅ እንጂ አቃለሁ ብላችሁ መገገም የለባችሁም:: ባለማችን ላይ የሚገኙ ስኬታማ ሰዎች እዚህ ደረጃ ሊደርሱ የቻሉት በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ባላቸው ፍላጎት ነው::
Translated by Google
Many people today are afraid to try something new. They prefer to be in their safe zone instead of trying something new. But according to a popular saying, being afraid to try something new is a big challenge. So in today's article, we have 5 new things to try every day.
1, To be yourself
Are you afraid that people will think differently about you just because you are open? Are you afraid that people will hate me? So let me tell you, the first reality of this life is that you should not expect everyone to love you. You are a rare and immaterial being. And everyone may not realize this. The most important thing is your attitude towards yourself. If someone does not like you, it is not your fault. But this does not mean that everything you think about yourself is right. It just shows that you are human.
Often people just make people happy. They give up on the other side to have fun and always have fun. But what you should not forget is that you have to maintain your true identity. Just because someone else didn't see the truth doesn't mean your price will go down. Your value is diminished when you do not show your true selves to others. And please be careful not to give up your true identity for the sake of people's happiness and satisfaction. And if you want your progress and your good side, then you are the only one who matters.
2, Helping people without pay
Life has many meanings. The way we interpret is only our own and our own. Happiness comes when we think outside of ourselves, not if we are the only ones. What many people don't understand in this life is that if we do good or bad in our lives, we will get paid. Practice giving love in your daily life without waiting for an answer. Give a lot to people who can't pay you back right now. Giving is not limited to money and material things. For example, smile at people who can't smile back at you. Encourage shy and cowardly people and give them morale. If you help other people find happiness in their life, you will see that happiness increases in your life.
3, Accept the consequences of your actions
How do you do when you make a mistake? Do you take responsibility or do you think about the person or circumstances around you? What many people don't understand about life is that if we take responsibility for what we have done in the past, we will inevitably achieve our dreams for the future. But if you post your current situation on other people, you will not want to take responsibility in the future. Excusing other things is a way of looking for nonsense. Making excuses for things is the first step to failure. Only you and I have to take responsibility for your decision. Some results may be unpleasant, but you should always say that it is my responsibility to make a difference every day. Because results are part of actions. If you take responsibility for your actions, you can make a big difference in yourself by learning something new.
4, Being open to the bad things we face
At some point, even people we trust may feel hurt. Our heart is broken. There may be times when you have broken someone else. Maybe at some point, you can fight with your friends. You may be fighting with your loved ones and you may be afraid that you will lose them. Or you may lose someone you love unexpectedly. These events are a part of life and we must accept them wholeheartedly. Many people find it difficult to open ourselves to things. Few people dare to face things. You may think it is good to keep your heart closed so that you do not feel sick. But to close one's heart is like not living. As long as anyone is alive and able to love, he will inevitably be hurt at some point. And opening your heart to these things will create sincerity and faithfulness in your life. So laugh and rejoice that nothing has touched you in your life. You should not be afraid that your day may end in pain, but you should fear that it may not start with love and loyalty. Life is short. You need to be open to different ailments and accept them wholeheartedly. Because being faithful to ourselves and facing trials will make us great.
5, Say I Can't Do What You Don't Know
Many people ruin many things by saying that they do not know what they do not know. To be honest, if you can't do something, what can you lose? Do your friends make fun of you? Or do you think that your dignity was degraded at that time? But you should know that you can only experience such experiences at that time. If you say no, you will get new information and new things, so you will expand your knowledge. Maybe your friends who are laughing at you don't know anything. Knowledge is something you can easily find. But this only happens when you ask. And if you want to grow and change in their life, you have to learn something new, not just pretend. Successful people on our planet have reached this point because they want to try new things every day.
0 Comments