10 የኩላሊት ህመም ምልክቶች | 10 Symptoms of kidney disease

photo of kidney


ኩላሊቶች ወደታችኛው ጀርባዎ የሚገኙ ጥንድ አካላት ናቸው በአከርካሪዎ  በያንዳንዱ ጎን አንድ ኩላሊት ይገኛል። ኩላሊቶች ደምን ለማጣራትና ከሰውነታችን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ይጠቅማሉ። ኩላሊት መርዛማ አካላትን ወደ ፊኛዎ ( የሽንት ማጠራቀሚያ ) ይልካል ይህም በኋላ ሰውነቶ በሽንት መልክ የሚያስወግደው ይሆናሉ።

ሰዎች በኩላሊት ህመም ጋር እየኖሩ ሳለ አብዛኞቹ ላያውቁት ይችላሉ። በርካታ የኩላሊት ህመም (በሽታ) አካላዊ ምልክቶች አሉ። ነገር ግን ሰዎች ከሌሎች ሁኔታዎች ጋር ያያይዙታል። እናም የኩላሊት ታማሚ መሆናቸውን የሚያውቁት:

  • ኩላሊታቸዉ ከአገልግሎት ውጭ ከሆነ በኋላ ወይም
  • ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን በሽንታቸው ውስጥ ሲገኝ ነው

 

የኩላሊት ህመም ምልክቶች: 

1, ድካምና የማትኮር ችግር

2, የእንቅልፍ እጦት ችግር

3, ደረቅ የሚያሳክክ ቆዳ

4, በተከታታይ መሽናት

5, በሽንት ዉስጥ ደም ሲኖር

6, አረፋ ያለበት ሽንት

7, በዓይኖቾ አካባቢ የማያቋርጥ እብጠት

8, የቁርጭምጭሚቶ አና የእግሮቾ እብጠት

9, የምግብ ፍላጎት መቀነስ

10, የጡንቻ መሸማቀቅ

 


ምንም እንኳ አንድ ሰው የኩላሊት ህመምተኛ መሆኑን የሚያውቀው በምርመራ ቢሆንም እኚህ 10 ምልክቶች ግን የኩላሊት ህመምተኛ መሆኑን ሊጠቁሙ የሚችሉ ናቸው። በተጨማሪም ከፍተኛ የደም ግፊት የስኳር በሽታ በቤተሰብ ውስጥ የኩላሊት ታማሚ ካለ ወይም  ከነበረ ወይም 60 ዓመት በላይ ከሆኑ ለኩላሊት ህመም በየዓመቱ መመርመሮ በጣም ጠቃሚ ነው። እናም የሚሰሞትን የትኛውንም ዓይነት ስሜት ከዶክተሮቾ ጋር መመካከር ይኖርቦታል።

በመቀጠል ከላይ የተዘረዘሩትን በጥልቀት የምንመለከት ይሆናል። መልካም ንባብ!


1, ድካም እና የማትኮር ችግር

image of a person tired


የኩላሊት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መርዛማ እና ያልተጣሩ ንጥረ ነገሮችን በደም ውስጥ እንዲከማች ሊያደርግ ይችላል። ይህ ደግሞ ሰዎች ድካም እንዲሰማቸውና ነገሮችን በትኩረት እንዳይሠሩ ወይም ትኩረት እንዲያጡ ሊያደርጋቸው ይችላል።

ሌላኛው ላሊት ህመም ወይም በሽታ ተጓዳኝ ችግሩም የደም ማነስ ማስከተሉ ሲሆን ይህም ድካም እና አቅም ማጣት ሊያስከትል ይችላል።


2, የእንቅልፍ እጦት ችግር

a women yawning in bed photo


ኩላሊቶቾ በትክክለኛው መንገድ በማያጣሩበት ጊዜ መርዛማ ንጥረነገሮች ከሰውነቶ በሽንት በኩል መውጣት ይልቅ በደም ውስጥ ይቆያሉ። ይህ ለመተኛት አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል።

 ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች "የእንቅልፍ አፕኒያ" ለተባለ ችግር የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።

  • የእንቅልፍ አፕኒያ ማለት የእንቅልፍ መዛባት ሲሆን ካልታከሙት ከፍተኛ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ ለደም ግፊትና ለልብ ህመም ያጋልጣል.. የእንቅልፍ አፕኒያ በእንቅልፍ ወቅት አተነፋፈስ በተደጋጋሚ እንዲቆም ያደርጋል። ይህም ለሊቱን ሙሉ ማንኮራፋት እና ምንም እንኳን በቂ የሚባል የእንቅልፍ ጊዜ ቢያገኙም በቀን የድካም ስሜት እንዲኖሮት ያደርጋል።

3, ደረቅ እና የሚያሳክክ ቆዳ

photo of a Skin


ጤናማ ኩላሊቶች ብዙ ጠቃሚ ስራዎችን ይሰራሉ። መርዛማ እና አላስፈላጊ ፈሳሾችን ለማስወገድ ቀይ የደም ሴሎችን ለመስራት አጥንቶችን ለማጠንከር እና በደም ውስጥ ትክክለኛውን የማዕድን መጠን ለመጠበቅ ይሰራሉ።

ደረቅ የሚያሳክክ ቆዳ የማዕድናት አለመመጣጠን እና የአጥንት በሽታ አመላካቾች ሊሆኑ ይችላሉ። እኝህም በሽታዎች ለከፋ የኩላሊት ህመም የሚያጋልጡ ናቸው። እናም ኩላሊቶቾ የሚጎዱ ከሆነ የማዕድናትን እና የንጥረ ነገሮችን መጠን መጠበቅ ስለምያቅተው ለደረቅ እና ለሚያሳክክ ቆዳ ይዳረጋሉ።


4, በተከታታይ መሽናት

photo of a child peeing


በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት በተለይም በምሽት እየተነሱ  በተደጋጋሚ መሽናት የኩላሊት ህመም ምልክት ሆን ይችላል። የኩላሊት ማጣሪያዎች በሚጎዱበት ጊዜ የሽንት ፍላጎት መጨመር ሊያስከትል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሽንት ኢንፌክሽን ወይም በወንዶች የፕሮስቴት መስፋት ሊሆን ይችላል።

  • ፕሮስቴት ማለት በወንዶች የመራቢያ አንድ አካል ሲሆን, እሱም ብልትን ፕሮስቴትን እና የዘር ፍሬዎችን ያጠቃልላል።


5, በሽንት ውስጥ ደም ሲኖር

a photo of pee and blood


ጤናማ ኩላሊቶች በተለምዶ ሽንት ለመፍጠር ከደም ውስጥ ቆሻሻን (ያልተ ንጥረ ነገሮችን) ሲያጣሩ የደም ሴሎችን በሰውነት ውስጥ እንዲቀሩ ያደርጋሉ። ነገር ግን የኩላሊቱ ማጣሪያዎች ሲጎዱ እነዚህ የደም ህዋሳት ወደ ሽንት ሊገቡ ይችላሉ።

በሽንት ውስጥ ያለው ደም የኩላሊት በሽታን ከማመልከቱም በተጨማሪ ዕጢዎች የኩላሊት ጠጠር ወይም ኢንፌክሽንን ሊያመለክት ይችላል።


6, አረፋ ያለበት ሽንት

foamy pee photo


በሽንት ውስጥ ከመጠን በላይ አረፋ በተለይም ከመሄ ( ከመወገ ) በፊት ብዙ ጊዜ እንዲታጠ  የሚጠይቅ ፣ ውስጡ ፕሮቲን መኖሩን ያመለክታ አረፋው እንቁላል ለማዋሀድ በምትመቱ ጊዜ እንደሚያሳየው አረፋ ነው የሚመስለው። በተጨማሪም በሽንትና በእንቁላል ውስጥ የሚገኘው የፕሮቲን ዓይነት ( አልቡሚን ) ተመሳሳይ ነው።


7, በዓይኖቾ አካባቢ የማያቋርጥ እብጠት

swollen eye photo


በሽንት ውስጥ ያለው ፕሮቲን የኩላሊት ማጣሪያዎች መጉዳታቸውን የሚያሳይ የመጀመሪያ ምልክት ነው። ይህም ፕሮቲን ወደ ሽንት ውስጥ እንዲገባ ያስችለዋል። ይህ በዓይኖቾ ዙሪያ ያለው እብጠት ኩላሊቶ በሰውነቱ ውስጥ ከማቆየት ይልቅ በሽንት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን በመልቀቁ ምክንያት ሊሆን ይችላል።


8, የቁርጭምጭሚቶቾ እና የእግሮቾ እብጠት

a photo of swollen ankle


የኩላሊት አቅም ሲቀንስ ሶድየም የተባለውን ማዕድን ማስወገድ ሊያቅተው ይችላል። ይህም ግሮ ወይም ቁርጭምጭሚቶቾ ላይ እብጠት ያስከትላል።

በታችኛው የሰውነታችን ጫፎች ጋር እብጠት መኖሩ የኩላሊት ቅም ማነስ ብቻ ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ :

  • የልብ በሽታ
  • የጉበት በሽታ አና
  • ስር የሰደደ የእግር ደም ስር (ቧንቧ) ችግሮች ምልክት ሊሆን ይችላል።

9, የምግብ ፍላጎት መቀነስ

a photo of a food


ይህን ምልክት ለኩላሊት በሽታ (ህመም) ብቻ መውሰድ አይቻልም። ምክንያቱም የምግብ ፍላጎት መቀነስን የሚያስከትሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ። ለምሳሌ :

  • በባክቴሪያ እና በቫይረስ
  • ሀዘን ጭንቀት እና ድብርት
  • ጉንፋን
  • የስኳር ህመም
  • ካንሰር እና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ..

ነገር ግን በኩላሊት አቅም ማንስ ምክንያት መርዛማ ንጥረ ነገሮች መከማቸትም አንዱ የምግብ ፍላጎት እንዲቀንስ መንስኤ ሊሆን ይችላል።


10, የጡንቻ መሸማቀቅ

muscle cramp photo


የኤሌክትሮላይት (በኩላሊት ውስጥ ያሉ ማእድናት እና ንጥረ  ነገሮችን ያካትታል) አለመመጣጠን ኩላሊት ተግባር ዛባትን ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ ዝቅተኛ የካልሲየም እና የፎስፈረስ መጠን አለመመጣጠን ሊሆን ይችላል። እናም ይህ ለጡንቻ መሸማቀቅ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል።

 

በአጠቃላይ

ኩላሊት ማለት የሰውነታችን አንድ ክፍል ሲሆን ደምን ለማጣራትና ከሰውነታችን የማያስፈልጉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን አጣርቶ የሚያስወግድ ነው።

የኩላሊት ህመም ምልክቶቹ የተለያዩ እና ማወቅ የሚገባን አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። ነገር ግን መዘንጋት የሌለብን ነገር እኝህ ምልክቶች ለኩላሊት ህመም ብቻ ናቸው ብለን መውሰድ አንችልም። እናም በርግጠኛነት የኩላሊት ህመም (በሽታ) እንዳለብን ልናቅ  የምንችለው ምርመራ ካደረግን ብቻ ነው። ስለዚህ እባኮት ይህንን ግንዛቤ  ውስጥ በመክተት መፍትሔ ማግኘት ይችላሉ።


Translated by Google


The kidneys are a pair of organs in your lower back. There is one kidney on each side of your spine. The kidneys are used to filter blood and remove toxins from the body. The kidneys send toxins to your bladder, which the body then excretes in the form of urine.

While people are living with kidney disease, most people may not know it. There are many physical symptoms of kidney disease. But people associate it with other situations. And those who know they have kidney disease:

  • After their kidneys are out of use or
  • It is when a large amount of protein is found in their urine

 

Kidney disease symptoms:

  1. Fatigue and inattention
  2. Insomnia
  3. Dry and itchy skin
  4. Continuous urination
  5. When there is blood in the urine
  6. Foamy urine
  7. Persistent swelling around your eyes
  8. Swelling of the ankles and ankles
  9. Decreased appetite
  10. Muscle spasm


Although a person is diagnosed with kidney disease, here are 10 signs that you may have kidney disease. It is also important to get tested for kidney disease every year if you have high blood pressure, diabetes, or if you have kidney disease in your family or are over 60 years old. And you should consult your doctor about any feelings you may have.

We will then take a closer look at the above. Happy reading!


1, Fatigue and inattention

Significant renal failure can lead to the accumulation of toxins and unrefined substances in the blood. This can make people feel inferior and inactive.

Another complication of kidney disease is anemia, which can lead to fatigue and weakness.


2, Insomnia

When your kidneys do not filter properly, toxins remain in the bloodstream instead of in the urine. This can make sleeping difficult.

People with chronic kidney disease are more prone to sleep apnea.

  • Sleep apnea is a sleep disorder that can lead to serious health problems if left untreated. For example, it can lead to high blood pressure and heart disease. Sleep apnea can cause shortness of breath during sleep. This can cause you to snore all night and get tired during the day even if you get enough sleep.


3, Dry and itchy skin

Healthy kidneys do many important things. They work to remove toxins and unwanted fluids, build red blood cells, strengthen bones, and maintain the right amount of minerals in the blood.

Dry and itchy skin can be a sign of mineral deficiency and bone disease. These diseases can lead to more severe kidney disease. And if your kidneys are damaged, you will not be able to control the number of minerals and nutrients, which can lead to dry and itchy skin.


4, Continuous urination

Frequent urination, especially at night, can be a sign of kidney disease. When kidney filters are damaged, urinary incontinence can increase. Sometimes it can be a urinary tract infection or an enlarged prostate in men.

The prostate is a part of the male reproductive system that includes the penis and testicles.


5, When there is blood in the urine

Healthy kidneys normally filter out impurities from the blood to produce urine, leaving blood cells in the body. However, when the kidney filters are damaged, these blood cells can enter the urine.

Blood in the urine may indicate kidney disease and may indicate tumors, kidney stones, or infections.


6, Foamy urine

Excess foam in the urine, especially if it needs to be washed several times before it is excreted, indicates the presence of protein in it. The foam looks like foam when you beat it to combine eggs. The same type of albumin is found in urine and eggs.


7, Persistent swelling around your eyes

The protein in the urine is the first sign that the kidneys are damaged. This allows the protein to enter the urine. This swelling around the eyes may be due to the release of large amounts of protein into the urine, rather than by the kidneys.


8, Swelling of your ankles and feet

When the kidneys fail, they may not be able to eliminate sodium. This can cause swelling in your legs or ankles.

Swelling of the lower extremities may not be the only cause of kidney failure. example :


  • Heart disease
  • Liver disease And
  • It can be a sign of chronic vascular problems.


9, Decreased appetite

This symptom is not limited to kidney disease. Because there are many reasons why appetite can be reduced. example :


  • Bacteria and viruses
  • Sadness, anxiety, and depression
  • Flu
  • Diabetes
  • It could be cancer and the like.

However, the accumulation of toxins due to kidney failure can also lead to reduced appetite.


10, Muscle Cramp 

Electrolyte imbalance (including minerals and nutrients in the kidneys) can lead to impaired kidney function. For example, low levels of calcium and phosphorus may be impaired. And this can contribute to muscle cramps.


As a whole

The kidneys are a part of the body that cleanses the blood and removes unwanted toxins from the body.

The symptoms of kidney disease are varied and important to know. But we must not forget that these symptoms are only for kidney disease. And we can only know for sure if we have kidney disease by conducting a medical examination. So please be aware of this and find a solution.

Post a Comment

0 Comments