ወላጆቻችሁን በእድሜ ሲገፉ ውደዷቸው እናም አክብሯቸው ምክንያቱም… | Respect your parents

ከስር ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ😀





የ 80 ዓመት አዛውንት በከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ከሚገኘው፣ 45 አመት ከሆነው ልጃቸው ጋር በመሆን በቤቱ ሶፋ ላይ ተቀምጠው ነበር ፡፡ በድንገት አንድ ወፍ መስኮቱ ማንቋቋት ጀመረች ፡፡ አባትየው ልጁን “ይህ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው ፡፡ ልጁም “አንድ ወፍ ናት” ሲል መለሰ ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አባትየው 2 ኛ ጊዜ ልጁን “ይህ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው ፡፡ ልጁም “እንዴ አባዬ አሁን እኮ ነግሬህ ነበር፣ ወፍ ናት” አለው ፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ አዛውንቱ አባት 3 ኛ ጊዜ ልጁን “ይህ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው ፡፡ በዚህን ጊዜ ልጁ ለአባቱ ወፍ ናት ብሎ ለአባቱ ሲናገር አንዳንድ የመበሳጨት ስሜት ተሰማው ፡፡ እናም እንዲህ ሲል መለሰ “ወፍ ፣ ወፍ ፣ ወፍ ነው” ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባትየው ልጁን ለ 4 ኛ ጊዜው “ይህ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ አባቱ ላይ በመጮህ ፣ “ደጋግሜ የነገርኩህ ቢሆንም ፣ ደጋግመህ ለምን ተመሳሳይ ጥያቄ ትጠይቀኛለህ?" አለው ። ትንሽ ቆይቶ አባትየው ወደ ክፍሉ ሄዶ ልጁ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ጠብቆ የቆየውን ያረጀ የድሮ ማስታወሻ ደብተር ይዞ መጣ ፡፡ አንደኛውን ገጽ ገልጦ ልጁ ያንን ገጽ እንዲያነበው ጠየቀው ፡፡ ልጁ ሲያነበው የሚከተሉትን ቃላት በማስታወሻ ደብተር ውስጥ ተጽፈው ነበር ፣ 



Photo of a old man and child hands



“በዛሬው እለት ሦስተኛ ዓመቱን ከያዘው ትንሹ ልጄ ጋር ሶፋ ላይ ተቀምጠን ሣለ አንድ ወፍ በመስኮት ላይ ተቀምጣ ነበር ፣ ልጄ ምን እንደሆነች 23 ጊዜ ጠየቀኝ ፣ እኔም ለአንድ ጊዜ እንኳ ሳልታክት ልጄን እየሳምኩት ደጋግሞ ለሚጠይቀኝ ጥያቄዎች በሙሉ መልስ ሰጠሁት። ትንሹ ልጅ 23 ጊዜ “ይህ ምንድን ነው?” ብሎ ሲጠይቀኝ ፣ በጭራሽ አልተበሳጨሁም።  አባትየው ተመሳሳይ ጥያቄን ለ 23 ጊዜ ሲመልስ ምንም አልተበሳጨም ነበር ፡፡ ዛሬ ግን አባትዬው ለ 4 ጊዜ ልጁን ሲጠይቀው ልጁ ተበሳጭቶ እና ተናዶም ነበር ፡፡ ስለዚህም ፣ ወላጆችዎ ወደ እርጅና ከደረሱ እነሱን መግፋት ወይም እንደ ሸክም አይቁጠሯቸው ።  ደግነት የተሞላበት ቃል ይናገሩ ፣ አሪፍ ፣ ጨዋ ፣ ትሑትና ደግ ይሁኑላቸው ፡፡ ለወላጆችዎ ትኩረት ይስጡ ፡፡ ለዛሬ ይህን ጮክ ብላቹሁ ተናገሩ “ወላጆቼ ለዘላለም ደስተኛ ሆነው ማየት እፈልጋለሁ ፡፡" ወደ ፈጣሪ በመጸለይ "ወላጆቼን በተሻለ መንገድ አገለግላለሁ ፡፡ ለወላጆቼ ጥሩ እና ደግ ቃላትን ሁሉ እናገራለሁ ፡፡"


Translated by Google


The 80-year-old was sitting on the couch at home with his 45-year-old son in high school. Suddenly, a bird began to peek out of the window. “What is this?” Asked the father. He asked. "It is a bird," replied the boy. A few minutes later, the father asked his second son, "What is this?" He asked. The boy said, "Dad, I just told you, she's a bird." Shortly afterward, the old man asked his son, "What is this?" He asked. He was upset when he told his father that he was a bird. And he replied, "Bird, bird, bird." Shortly afterward, the father asked his son, "What is this?" He asked. The boy shouted at his father, "I have told you so many times, but why do you ask me the same question over and over again?" ፡ When the boy was reading, the following words were written in a notebook:


“Today, while I was sitting on the couch with my third-year-old son, a bird was sitting on the window sill. “What is this?” 23 times. I was not upset at all. The father did not get upset when he answered the same question 23 times. Today, the father is upset and angry when his father visits him four times. Therefore, do not push or shove your parents into adulthood. Speak kindly, be kind, gentle, humble, and kind. Pay attention to your parents. Say it out loud today: "I want to see my parents happy forever." I pray to the Creator, "I will serve my parents better." I say good and kind words to my parents. "



Post a Comment

0 Comments