ደም የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ነው። ለመኖራችን ወሳኝ በመሆኑ፣ በጤና መኖራችን ወይም በሽተኛ መሆን፣ የአእምሮአችንን ጥንካሬም ሆነ ድክመት የሚስጥሩ ብቸኛ ቁልፍ የምናገኘው በዚሁ የደማችን አይነት ነው። ይኀውም የደም አይነታችን (blood type) ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆነውን የምግብ አይነትና ውጥረትን ለመቋቋም የምንወስደው እርምጃን ይወስናል ማለት ነው።
የደም አይነት ከምግብ ጋር ያለው ዝምድና
በየጊዜው የሚለዋወጥ ሳይሆን ቋሚ የሆነ ኬሚካላዊ ቅንብር ይዞ ከመፈጠር እስከ ሞት ድረስ አብሮ የሚጓዝ ነው። ለዘመናት ጤነኛ ወይም
በሽተኛ የመሆናችን ነገር ሚስጥር ከደማችን አይነትና የአመጋገብ ዘዴ ጋር መያያዙን ልብ ሳይባል ቆይቷል። የሚያስገርመው ነገር ሰውነታችን
ጤና በማይሰማበት ጊዜ የምግብ ፍላጎቱን ወደ ማማረጥ እንገባለን፣ ደማችንም በ አይነቱ እንዲቀርብለት ይፈልጋል። እንዲሁም በተጨማሪ
ልብ ብለን ካየን የተወሰነ የምግብ አይነት ለአንዳንድ ሰዎች መደበኛ ምግባቸው ሆኖ የሰውነታቸውን ክብደት በማስተካከል ጤናማና ንቁ
እንዲሆኑ ሲረዳቸው፣ ባንፃሩም ይኸው ምግብ እየተመገቡ የሰውነታቸው ሚዛን በየጊዜው እየጨመረና የሰውነታቸው ቅርፅም እየተበላሸ ድካም
የሚሰማቸውና በጭንቀት ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ናቸው። እናም ከላይ ወዳየነው አንድነት እና ልዩነት ውስጥ ስንገባ በቂ ግንዛቤ ኖሮን
በጥንቃቄ የአመጋገባችንን ዘዴ እንድናስብበት ይረዳናል። የደም አይነት ከመጀመሪያው የሰው ዘር ጀምሮ ለትውልድ በተፈጠረው የማያቋረጥ
ሰንሰለታዊ መስመር ይዞ እየተጓዘ ነው አሁን ወደምንኖርበት ወቅት የደረሰው፡፡ ስለዚህ የደም አይነት የማያረጅና የማይወድም የቅድመ
ዝርያዎቻችን የማይፋቅ የታሪክ አሻራ መዝገብ ነው፡፡
ከስር ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ😀
የምግብ እና የደም አይነት ግንኙነትና ልዩነት
ከ45 ዓመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሊገነዘቡት የቻሉ ዶክተር ጀምስ ዲ-አዳሞ የተባለው የስነምግብ ምሁርና
ተመራማሪ ነበሩ፡፡ እኝህ ተመራማሪ በሚሰሩበት ክሊኒክ
ውስጥ የተወሰኑ ሕመምተኞች ክሊኒኩ በሚሰጠው ለሕሙማን የተዘጋጀ ምግብ ፈጣን ለውጥ ሲያሳየው፣ ባንጻሩ ይኸው ምግብ በመመገብ ህክምና
የተደረገላቸው በጤንነታቸው ምንም ለውጥ ሳያሳዩ ይባስ ብሎም በአንዳንዶቹ ላይ በሽታው ሲጠናባቸው ታይቷል፡፡ ይህንን በማስተዋል
ምርምራቸውን በመጀመር ሰውነታችንን የሚመግብ ደም በመሆኑ፣ በደምና በምንበላቸው ነገሮች ላይ ያለው ዝምድናን ለማወቅ ግማሹን እድሜያቸው
በምርምር ላይ በማሳለፍ ለዚህ ውጤት በፋና ወጊነት ይጠቀሳሉ፡፡ በመቀጠልም የተለያየ የደም አይነት ያላቸው ሰዎች በአመጋገባቸው
ላይ ያለዉ አንድነትና ልዩነት በማጥናት የመጀመሪያው የሰው ዘር ደም ኦ(O) ባህሪ በማስቀደም የዚህ ደም አይነት
ባለቤት ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያላቸው ምግቦች በመመገብ በቀላሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምግቡን በማንሸራሸር ጤናማ ህይወት ሲመራ ባንፃሩ
ይህ ሰው ዝቅተኛ የፕሮቲን ይዘት ያላቸው ምግቦችን በሚመገብበት ጊዜ ሌላ ምልክት እናይበታለን ብለዋል ይሄው ከፍተኛ የኮምጣጤ ክምችት
በጨጓራው ውስጥ እንዲኖር ሲያደርግ የጨጓራው ግርግዳ በመሸንቆር እንዲሰቃይና በሽታ ላይ እንዲወድቅ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
የምግብ አይነቶች |
በመቀጠልም የሰው ዘር ወደ የእርሻ
ዘመን በተሽጋገረበት ወቅት የተፈጠረው የደም አይነት ኤ(A) ሲሆን የዚህ ደም አይነት ባለቤት የሆነ ሰው ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያላቸው
ምግቦችን በሚመገብበት ጊዜ በጨጓራው ውስጥ የሚመነጨው ኮምጣጤ (አሲድ) አነስተኛ በመሆኑ ምግቡን በቀላሉ ልያንሸራሽረው ስለማይችል
በጨጓራው ከበድ ያለ መብላላት ችግር ይፈጥራል፣ እንዲሁም ቀላል የሆኑ የአትክልት ፕሮቲኖች በሚመገብበት ጊዜ ጤነኛና ንቁ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም የእንሰሳት ተዋጽኦ (እርጎ፣ ወተት፣ ቅቤና የአይብ አይነቶች) አክታና ንፋጭ ይበዛበታል፡፡ ባአብዛኛው በጨጓራ ነቀርሳ
(ካንሰር) የሚጠቁ የኤ(A) የደም አይነት ባለቤት የሆኑ ናቸው ብለዋል፡፡
የስነአመጋገብ ምሁር የሆኑት የዶክተር ጀምስ ዲ.አዳሞ ልጅ ዶክተር ፒተር ጆይ.ዲ.አዳሞ
የአባታቸውን ምርምር መሰረት በማድረግ በስፋት መቀጠሉን ተያያዙት፡፡ በምርምራቸው የጥንት ሰዉ ከየት ተነስቶ እንዴት በዓለማችን
እንደተሠራጨና በየት አከባቢ አዲስ ተጨማሪ የደም አይነት እንደተፈጠረ፣ የሰው ልጅ በተሰደደባቸው ቦታዎች ሁሉ አዳዲስ የምግብ አይነቶች
መመገብ መጀመርና ያስከተለው ለውጥ አክለው ውጤታቸውን ቀላልና ግልጽ በሆነ መንገድ ለአላም አቀረቡለት፡፡
ምንጭ፡ የጤና ሚስጥራዊ ቁልፍ
Blood is the beginning of all creation. It is with this type of blood that we can find the only key to our health, whether we are healthy or ill. This means that our blood type determines the type of food and stress that is needed for our body.
Blood type's relationship with food does not change from time to time, but it does go hand in hand with its permanent chemical composition, from death to death. For centuries, the secret to being healthy has been linked to our blood type and diet. Surprisingly, when our body is not feeling well, we tend to crave food, and our blood needs to be supplied. Also, if we look at certain foods as a regular diet for some people and help them to stay healthy and active, many people who are eating the same food are constantly gaining weight and losing weight. And as we move into the unity and diversity that we have seen above, it helps us to have a proper understanding and to think carefully about our eating habits. The blood type has been going on since the first human race, in a series of generations. So blood type is an indelible mark on our ancestors' history.
The connection between food and blood type was first discovered 45 years ago by Dr. James D. Adamo, a nutritionist, and researcher. In the clinic where this researcher works, some patients have seen rapid changes in the diet provided by the clinic, while those who have been treated with the same diet have shown no improvement in their health, and in some cases, the disease has worsened. With this in mind, they began their research by devoting half of their lives to research the relationship between blood and what we eat, as it is the blood that feeds our bodies. Next, we study the similarities and differences in the diet of people of different blood types, prioritizing the characteristics of the first human blood O (O). "We will see another sign of the time," he said.
Next, human blood type A (A) is formed during the transition period of the human body. Eat simple vegetable proteins and stay healthy and active. Animal products (yogurt, milk, butter, and cheese) are also rich in sputum and mucus. Most people with gastric cancer have A blood type, he said.
0 Comments